እንኳን ወደ ድህረ ገፃችን በደህና መጡ!❤️ በዚህ ድህረ ገፅ ወቅታዊና መሰረታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ስለጎበኙን እናመሰግናለን፡፡ Welcome to our website! On this site, you will find basic information about fogera Woreda. Thank you for visiting us!
Image
አቶ ጌታቸው ገብሬ
አቶ ጌታቸው ገብሬ
የፎገራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
አቶ አንሙት ዘለቀ
አቶ አንሙት ዘለቀ

የፎገራ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ

ሙ/ታ አምሳል ማንደፍሮ
ሙ/ታ አምሳል ማንደፍሮ

የሳይንስና ቴክኖሎጅ ቡድን መሪ

Fogera Woreda 

Fogera is a woreda in Amhara Region, Ethiopia. Fogera is part of the Debub Gondar Zone. The district is bordered on the south by Dera, on the west by Lake Tana on the north by the Reb which separates it from Kemekem, on the northeast by Ebenat, and on the east by Farta.

The administrative center for this woreda is Wereta City. Other cities in Fogera include Alem Ber city.

ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቡድን

ፎገራ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቡድን መሰረታዊ ኮምፒዩተር ለ3ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

የፎገራ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ቡድን ለመምህራን ለ10 ተከታታይ ቀን ሲሰጥ የቆየው መሠረታዊ ኮምፒውተር እና የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የወረደው ብልፅግና ኃላፊ አቶ አስማማው ብርሃኑ ፣የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንሙት ዘለቀ እና የወረዳው ትምህርት ጸ/ቤት ኃለፊ አቶ ይበልጣል ጓዴ ተገኝተው መልዕክት ካስተለላፉ በኋላ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በጥሩ ሁኔታ ተጠናቋል።

የፎገራ ወረዳ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ቡድን
የፎገራ ወረዳ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ቡድን

በICT ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች አስመረቀ።

Image

2ኛ ዙር የመሰረታዊ ኮምፒውተር ስልጠና ማጠያቀቂያ መርሃግብር

የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችሉትን ነጻ የኦንላይን ስልጠና እድሎችን በዚህ ሊንክ የሚያገኙ ሲሆን https://ethiocoders.et/ ወይም በዚህ አፕ ይጠቀሙ፡፡

አዋጅ ቁጥር 296/2017 ዓ.ም

==============

“በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ማቋቋሚያ፣ ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 296/2017 ዓ.ም” ተብሎ በአማራ ክልል ምክር ቤት ጸድቆ ስራ ላይ ውሏል፤ ለመሆኑ አዋጁ ስለ ቢሮው መቋቋምና ስለ አዋጁ አስፈላጊነት ምን ይላል?


1. ቴክኖሎጂ ለሀገራዊ እድገት ከመሬት፣ ካፒታልና ከሰው ኃይል በመቀጠል ትልቅ ሚና የሚጫወትና አስፈላጊ ማሳለጫ መንገድ ከመሆኑም ባሻገር ጥንቃቄ ከጎደለው ደግሞ በአንፃሩ የሚያስከትለው ጉዳት ቀላል ስላልሆነ፤ የክልሉ መንግሥት ቴክኖሎጂን ሲያለማ፣ ሲያሸጋግር ወይም ግዥ ሲያስብ አዋጭነቱን፣ ታዳሽነቱንና የሚያስከትለውን የጎንዮሽ ጉዳት ታሳቢ ማድረግ የሚገባው ከመሆኑም በላይ የቴክኖሎጂ ፍላጎትና አቅርቦት እንዲሁም ቁጥጥሩን በማዕከል ደረጃ ማድረግ፣ የቴክኖሎጂ መረጣ፣ ልማትና ሽግግር ያለውን ፋይዳ በመረዳት ማስቀጠል፣ ጉዳቱን ደግሞ በመቀነስ ችግር ፈች የሆነና ወቅቱን ያገናዘበ ሕግና ሥርዓት ማበጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

2. ውጤታማ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ክልሉ ለማስገባት፣ ለማላመድና ለመጠቀም እንዲሁም በሚገባ አልምቶ የክልሉን ኢንዱስትሪያዊ ዕድገት በሳይንሳዊ ምርምሮች ለመደገፍ የሚያስችል ሆኖ በሀገር ደረጃ የተቀረፀውን ብሔራዊ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂና የኢኖቬሽን ፖሊሲ በክልሉ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዝ አቅም መፍጠር ተገቢ በመሆኑ፤

3. በክልሉ ውስጥ ለሚመረቱ ምርቶችና ለሚሰጡ አገልግሎቶች ውጤታማነትንና ተወዳዳሪነትን የሚያሳድጉ ቴክኖሎጂዎችን በማልማትና በማስፋፋት የግልና የመንግሥት ተቋማት፣ ሕዝብና መንግሥት በቂ፣ ወቅታዊና ጥራት ያለው መረጃ በማግኘት የአገልግሎት አሰጣጣቸውን በጥራትና በፍጥነት ማቅረብ እንዲችሉ አግባብ ካላቸው የፌደራል መንግሥት አካላት ጋር የጋራ ቅንጅታዊ አሠራርን በማስፈን አስተማማኝ የሆነ የቴክኖሎጂ መሠረተ-ልማት በመዘርጋት ለክልሉ ሁለንተናዊ ልማት መፋጠንና ለመልካም አስተዳደር መጎልበት በዕውቀትና በመረጃ ላይ የተመሠረተ አንድ ኢኮኖሚያዊ ማኅበረ-ሰብ መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

4. የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂው ዘርፍ እንደ አንድ ክፍለ-ኢኮኖሚ ተለይቶ መልማት በሚገባው ደረጃ እንዲበለፅግና በክልሉ ልማት ረገድ በመስኩ የተሠማራው የግል ዘርፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲያበረክት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸትና በዚሁ ዙሪያ የሚገኘውን ዕውቀትና መረጃ አይነተኛ የዕድገት መሳሪያ አድርጎ መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

5. የክልሉ ሕብረተሰብ ከዓለም አቀፍ ዕውቀትና ከየዕለቱ የመረጃ ፍሰት ተጠቃሚ የሚሆንበትን ዕድል በመፍጠርና በሀገራዊ ጉዳዮች ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ተሳታፊ በማድረግ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደሩን ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችልና በሳይንስና ቴክኖሎጂ በቂ የሙያ ዕውቀትና ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ማፍራት በማስፈለጉ፤

6. የክልሉ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት በተቀናጀ ሁኔታ በሥራ ላይ ውሎ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመዘገብ ዘርፉን ወጥነት ባለው መንገድ የሚያስተባብር፣ የሚደግፍ፣ አፈፃፀሙን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማከናወን የአገልግሎት ስታንዳርድ በማዘጋጀት ሁሉንም ተግባራትና እንቅስቃሴዎች በቅርብ የሚከታተልና ጥራቱን የሚቆጣጠር ራሱን የቻለ አካል ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት በተሻሻለዉ የብሔራዊ ክልላዊ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ አንቀጽ 39 ንዑስ አንቀጽ 3/ 1 ድንጋጌ ስር በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የቢሮውን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 296/2017 ዓ.ም አዉጥቷል።

አድቫንስድ ስልጠና
አድቫንስድ ስልጠና
ቴክኖሎጅ ስልጠና
ቴክኖሎጅ ስልጠና

Who is Online

We have 10 guests and no members online

Log in